Friday, June 19, 2020

የፀሎት ቦታ በቤታችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ስነስራዓት

የፀሎት ስፍራ በቤታችን የፀሎት ቦታ እቤት ዉስጥ ንጹህ ወደ ምስርቅ የሚያመላከት የጽሎት ቦታ ማዘጋጀት። 
 • ዋናው መፀለይ እና መስገድ መጀመር ሲሆን ቀስ በቀስ የፀሎቱን ቦታ ማስፋት እና ማሻሻል ይቻላል። 
 • ስፍራዉ ላይ የጥጥ ምንጣፍ ማዘጋጅት። • እዚ ጽሎት ቤት ዉስጥ መፀለይ፣ መስገድን እና የፀሎት መጽሓፍትን ማንበብ። 
 • ዋናው መፀለይ እና መስገድ መጀመር ሲሆን ቀስ በቀስ የፀሎቱን ቦታ ማስፋት እና ማሻሻል ይቻላል። 

 ይህንን ቦታ በአባቶች የተሳለ፡ 
 • የመድሓንያ አለምን፣ 
 • የቅድስት ማርያምን 
 • እና የቁሳን የመላእክቶችን ምስል በክብር በነጠላ ሸፍኖ ማስቀመጥ። 
 • አላማዉ ሃሳባችን እንዲሰበሰብና ተመስጦ እንኖረን ነዉ። ከምስሎቹ ስር 
     • መጽሓፍ ቅዱስ፣ 
     • ፀበል፣ 
     • የወይራ ዘይት፣ እምነት፣ 
     • ዕጣን 
     • ንፁህ ሽቶ 
     • እና ገድሎችን ማስቀመጥ። 

 ስግደት 
    • የአምልኮ ስግደት ፟ ለእግዚአብሔር ብቻ ሰዉነታችን፣ ጉልበታችን፣ ግንባራችን እና ሃሳባችን አንተ አምላክ ነህ እያለ እንሰግዳለን። 
• የፀጋ ስግደት ፟ ለመቤታችን ብቻ። ከወገባችን ዝቅ ብለን። 
• የክብር ስግደት ፟ ለቅዱስ መላእክት እና ለሰማእታት ከአንገታችን አጎንብሰን። 

 ስንጃምር ቤተሰቡ በአንድነት ፀሎት ቦታ ውስጥ ቢያንስ በቀን አንድ ግዜ መፀለይ እና መስገድ። ቢያንስ አቡነ ዘበሰማያትን (የዘወትር ፀሎት) በየእለቱ መፀለይ። እየለመድን ስንመጣ ሌሎችን የጽሎት መጻሃፍትን በህብረት ማንበብ፣ መፀለይ እና መስገድ። ቀስበቀስም በመከተለዉ ሁኔታ ማጠናከር። • ስዕሎቹ ቅብአ ቅዱስ ይቀባሉ ተፀልዮባቸው፡፡ 
     • የእመቤታችን፣ የቅዱስ ሚካኤል እና የቅዱስ ገብርኤል በግራና ቀኝ በመምበርከክ በግምባር ልክ ማስቀመጥ፡፡ 
     • መቆም ደግሞ የመድኃኔ ዓለም እና የሥላሴ ስዕል ይደረጋል፡፡ 
     • ከስዕሉ የመጽሐፍ መግለጫ ያህል ነው ራቅ የሚባለው፡፡ 
     • ቢቻል ቢቻል ቤተ ክርስቶያን ተባርካው በቅዳሴ ግዜ ቅብአ ቅዱስ ተቀብተው ቢመጡ ጥሩ ነው። 
     • በጥሩ ፍሬም መሰራት አለባቸው፡፡ • 

ከምስሎቹ ስር የፀሎት ውሃ፣ እጣን፣ የቤተ ክርስትያን እምነት፣ የወይራ ዘይትማስቀመጥ። 
    • የመጽሐፍት ማስቀመጫ እዛው ስዕሉ ሥር መኖር አለበት፡፡ ፀሎት ቤት ውስጥ ስለሚቀመጡት    የፀሎት ቁሳቁስ አንደኛው የፀሎት ውሃ፡- 
    • የፀሎት ውሃ የቅዳሴ ፀበል ውሃ ጠብ ሊደረግበትም ይችላል፡፡ 
    • ሌላም ጠበል ሊሆን ይችላል፡፡ አልያም ፍፁም ንፁህ ውሃ ሊሆን ይችላል፡፡ 
    • በምንፀልይበት ግዜ እፍ እንለዋለን፡፡ 
    • ምክንያቱም ቃለ እግዚአብሔር ይደርበት፣ የተባረከ ይሁን ማለት ነው፡፡ 
    • የፀሎቱ መንፈስና ኃይል በፀሎት ውሃው ላይ በሚያርፍበት ግዜ ያ እጅግ በጣም የተለየ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ሁለተኛ እምነት፡- 
     • እምነት መስዋዕት የቀረበበት፣ የዕጣን ማሳረግያ የተከናወነበት ሲሆን፡፡ 
     • ቤተ መቅደሱን ዞሮ፣ ታቦቱን ዞሮ፣ ልዑል እግዚአብሔርን እያመሰገነ የተማፀነበት፣ ስለ ህዝቡ ሐጥያት ስርየት የተደረገበት ነው፡፡ 
     • ስለዚህ ከቅዳሴ በኋላ ያለ እምነት ወስዶ ፀሎት ቦታ ላይ ማስቀመጥ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ሦስተኛ ዕጣን፡- 
 o ለአግዚአብሔር የሚቀርብ ስጦታስለሆነ ነው። 
 o ማቲዮስ 2፤ 11 o ሶስቱ የጥበብ ሰዎች ጌታ በተወለደ ግዜ እንዳቀረቡለት አራተኛ የወይራ ዘይት፡-
 • የወይራ ዘይት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ቦታዎች ላይ በመንፈሳዊ ተስፋ ይታወቃል፡፡ • በመዝሙር 22 ላይ ‹‹ራሴን በዘይት ቀባሁ›› ይላል፡፡ 
 • የወይራ ዘይት ደግሞ ማንኛዉም ክርስትያን የሚጠቀምበት ነው፡፡ 
 • እግዚአብሔርን አመስግኖ፣ እፈ ብሎ በራሱ የፀሎት ባርኮት ውስጥ ሊጠቀሙበት ይቻላሉ፡፡ በሃየማኖት እየበረታን ስንመጣ እናዚህን የፀሎት ሰዓታትን ማክበር፣ የፀሎትና እና የስግደት ስርዓት አቡነ ዘበሰማያት እና የቅድስት ማርያምን ፀሎት መድገም 

1. በመንፈቀ ሌሊት (12:ዐ0AM) 
2. በ11ሠዓት (5:00 AM) ዌዳሴ ማርያም፣ ሰይፈ መለኮት፣ ሠይፈ ሥላሴ 
3. በ3 ሠዓት (9:00 AM) አርጋኖን፣ መልክአ ገብርኤል፤ 
4. በ6 ሠዓት (12:00 PM) መልክአ ስላሴ፣ መልክአ ሚካኤል፤ 
5. በ9 ሠዓት (3:00 PM ) መልክአ መድኃኒዓለም፣ መልከአ ኡራኤል፤ 
6. በ11 ሠዓት (5፡00PM) 
7. በ3 ማታ (9:00 PM) 

መልክአ ሩፋኤል፣ አርጋኖን፤ የዘወትር የአምልኮ ስግደት፦ (መቅረት የሌለበት) የዉዳሴ ማርያም መጸሃፍ ላይ ያለዉን የዘወትር ጸሎት መፀለይ ይገባል። 
 • ለአብ እሰግዳለሁ፣ 
• ለወልድ እሰግዳለሁ፣
• ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ፣ 
• ምስጋና ይሁን ለአብ፣ 
• ምስጋና ይሁን ለወልድ፣ 
• ምስጋና ይሁን ለመንፈስ ቅዱስ፣ 
• በረከቱን ለሰጠን፣ ኃይሉን ላበዛልን፣ በዚህ ሠዓት ላቆመን፣ በቸርነቱ መንገድ ለመራን፣ በዚህ ሠዓት በፀጋ ለጠበቀን፣ በብርሃኑ ኃይል ለመራኸን፣ ላንተ፥ ክብር ምስጋና ይግባኽ፤ 
• ሃሌ ሉያ ለአብ፣ 
• ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ 
• ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ፤ 
• ቅዱስ እግዚአብሔር፣ 
• ቅዱስ ኃያል፣ 
• ቅዱስ ሕያው፣ 
• ቅዱስ ኤልሻዳይ፣ 
• ቅዱስ አዶናይ፣ 
• ቅዱስ ያህዌ፣ 
• ቅዱስ ፀባኦት፣ 
• ቅዱስ ኢየሱስ፣ 
• ቅዱስ ክርስቶስ፣ 
• ቅዱስ አማኑኤል፣ 
• የድንግል ማርያም ልጅ፤ ክብር ምስጋና ይግባው!። የንስሐ (ምህራት የመጠየቂያ) ስግደት፦ 
• ኪርያ ላይሶን ኢየሱስ፣ 
• ኪርያ ላይሶን ክርስቶስ፣ 
• ኪርያ ላይሶን አማኑኤል፣ 
• አቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረን፣ 
• አቤቱ አምላክ ሆይ ማረን፣ 
• አቤቱ መድኃኒዓለም ሆይ ማረን፣ 
• አቤቱ የድንግል ማርያም ልጅ ሆይ ማረን!። የፀጋ ስግደት፦ 
• ለድንግል ማርያምም እሰግዳለሁ፣ ክብር ምስጋና ይገባሻል። ይሄ የፀጋ ስግደት ነው፡፡ ፀጋ የተቀበለች ስለሆነ፡፡ የክብር ስግደት፦ 
• ለቅዱስ ሚካኤል እሰግዳለሁ፡፡ ይሄ ለጥበቃውና ለክብሩ፡፡ የእርሱን ክብር የፀሎት የምስጋና፣ የጥበቃዉን ክብር ለማግኘት፡፡ የክብር ስግደት ነው፡፡ የፀሎቱን ቦታ ሱባኤ ለበግባት መጠቀም እንችላለን።

No comments: